ሳይታጠብ እስከ አንድ ወር የሚቆይ አዲስ ቲ-ሸርት ለገበያ ቀረበ

ADDIS_NEWSneutral2026-08-04 12:19:54 UTC
AdYour ad here[email protected]

ሳይታጠብ እስከ አንድ ወር የሚቆይ አዲስ ቲ-ሸርት ለገበያ ቀረበ አሜሪካዊው የልብስ ኩባንያ ‘ሄርክሊዮን’ ያለ ምንም እጥበት እስከ አንድ ወር ድረስ መጥፎ ጠረን ሳይይዝ በየቀኑ መልበስ የሚያስችል "HercShirt V5.0" የተሰኘ አዲስ ቲ-ሸርት ለገበያ ማቅረቡን አስታውቋል። ኩባንያው ለዚህ ፈጠራው መዳብ፣ ብር፣ ዚንክ፣ ወርቅ እና የእሳተ ገሞራ አመድን ጨምሮ ሰባት ልዩ ንጥረ ነገሮችን በጨርቁ ክር ውስጥ ማካተቱ ተገልጿል ። እነዚህ ንጥረ ነገሮች ባክቴሪያዎችን ያግዳሉ፤ እርጥበትንም በመምጠጥ ልብሱ ምንጊዜም ይዘቱን ጠብቆ እንዲቆይ ያደርጋሉ ተብሏል። አልፎ አልፎ ብቻ ስለሚታጠብ ከሰባት መደበኛ ቲ-ሸርቶች በላይ ያገለግላል የተባለው ይህ ምርት በ79 ዶላር ይሸጣል። በተጨማሪም አቅማቸው አነስተኛ ለሆኑ ደንበኞች ለሶስት ቀናት የሚቆይ የ39 ዶላር አማራጭ እና እስከ ሁለት ሳምንት…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]