በደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር የተመረቁ የጸጥታ ኀይሎች ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ተዘጋጅተዋል።

AMHARAMASSMEDIAneutral2026-08-04 12:19:55 UTC
AdYour ad here[email protected]

በደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር የተመረቁ የጸጥታ ኀይሎች ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ተዘጋጅተዋል። በደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥና ለሀገዊ ተልዕኮ ዝግጁ ለመሆን ሲሠለጥኑ የቆዩ የደጀን ኀይል የፀጥታ አባላት ተመርቀዋል። ​ዘላቂ ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት በደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ለተከታታይ ቀናት ሲሠለጥኑ የቆዩ ጥምር የፀጥታ ኃይሎች ሥልጠናቸውን አጠናቀው ተመርቀዋል። ተመራቂዎች ​የሀገርን ነፃነትና ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ታሪካዊ አደራን የመጠበቅ ኀላፊነት እንዳለባቸው ተመላክቷል። የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር አብራራው አበጀ እና የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ሚሊሻ መምሪያ ኀላፊ ብሩክ አለምነው በምረቃ ፕሮግራሙ ተመራቂዎችን አበረታተዋል። መረጃው የ​ደብረ ታቦር ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው።…

Read the full story at amharamassmedia ↗
AdYour ad here[email protected]