ዩክሬን በፈፀመችው የድሮን ጥቃት ሰባት ሰዎች ሲገደሉ 40 ያህል መቁሰላቸውን ሩሲያ አስታወቀች
ዩክሬን በፈፀመችው የድሮን ጥቃት ሰባት ሰዎች ሲገደሉ 40 ያህል መቁሰላቸውን ሩሲያ አስታወቀች በደቡባዊ ሩሲያ በሚገኝና በሰዎች በተጨናነቀ የባህር ዳርቻ ላይ ዩክሬን በፈፀመችው የድሮን ጥቃት ሦስት ህጻናትን ጨምሮ ሰባት ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታወቁ።ጠቅላላ የቆሰሉት ሰዎች ቁጥር 40 ደርሷል፣ 17 ሰዎች ደግሞ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል ሲሉ የክራስኖዳር ክልል ገዢ ቬኒያሚን ኮንድራቲዬቭ ተናግረዋል። ዩክሬን "በሲቪሎች ላይ ሆን ብላ የፈፀመችው ጥቃት" ሲሉ ገዢው ከሰዋል። ዩክሬን ስለ ጥቃቱ ምንም አስተያየት አልሰጠችም። ሁለቱም ወገኖች ሆን ተብሎ በሲቪሎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃትን ከፈፀሙ በኃላ ስል ድርጊቱ ይክዳሉ። ድሮኑ ምን ኢላማ እንዳደረገ ግልጽ አይደለም። አንዳንድ የዩክሬን የቴሌግራም ቻናሎች በኤሌክትሮኒክ ጦርነት ምክንያት በባህር ዳርቻ ላይ እንደወደቀ…
Read the full story at zena24now ↗