ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው አልባሳትን የሰረቁ 6 ግለሰቦች ተያዙ‼

WASULIFEneutral2026-08-04 15:26:44 UTC
AdYour ad here[email protected]

ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው አልባሳትን የሰረቁ 6 ግለሰቦች ተያዙ‼ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 (መቻሬ ሜዳ አካባቢ) ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 9 ሰዓት ላይ የቪትስ ተሽከርካሪ በመጠቀም የአንድ አልባሳት መሸጫ ሱቅ ሰብረው በመግባት ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የወንዶች ሱሪዎች፣ ጫማዎች እና ቲሸርቶች የሰረቁ 6 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ፖሊስ ገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ በህዝብ እና በፖሊስ ትብብር የተያዙ ሲሆን፣ በተጨማሪም ከሌሎች ቦታዎች የሰረቋቸው የጎማ ጎሚኒ እና የኤሌክትሪክ ኬብሎች ከእነሱ ጋር ተይዘዋል። ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ ክስ ለማስመስረት እየሰራ ይገኛል። መረጃው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ነው #WasuMohammed video 👇Like + Follow👇…

Read the full story at wasulife ↗
AdYour ad here[email protected]