በፋብሪካ የሚመረቱ አልኮሎች ዋጋ በመጨመሩ የጠጅ ፣ ጠላና አረቄ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከፍ ብሏል ተባለ
በፋብሪካ የሚመረቱ አልኮሎች ዋጋ በመጨመሩ የጠጅ ፣ ጠላና አረቄ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከፍ ብሏል ተባለ በፋብሪካ የሚመረቱ አልኮሎችና ትንባሆ ላይ የኤክሳይዝ ታክስ መጣል የምርቶቹን ዋጋ አንዲጨምር በማድረጉ የምርቶቹ የተጠቃሚዎች ቁጥር መቀነሱን ጥናት አሳየ፡፡ በሌላ በኩል ግን ጠጅ ፣ ጠላ ፣ አረቄ የመሳሰሉት ምርቶች ተጠቃሚያቸው መብዛቱን በጥናቱ ግኝት ተጠቅሷል፡፡ ጥናቱን ያጠናው በጤናው መስክ ጥናትና ምርምሮችን የሚያካሂደው ፍኖት የተሰኘ ድርጅት ነው ። ድርጅቱ ይህን ጥናት ይፋ ያደረገው ከስድስት ዓመት በፊት በአልኮል እና በትንባሆ ላይ የተጣለው ኤክሳይዝ ታክስ ምን ውጤት እንዳመጣ በአማራ፣ኦሮሚያና በአዲስ አበባ ላይ ያካሄደው ዳሰሳዊ ጥናት ነው ። በአልኮልና በትንባሆ ምርቶች ላይ የተጣለው ኤክሳይዝ ታክስ የተጠቃሚዎችን ቁጥር ከ10 እስከ 20 በመቶ እንዲቀንስ አድርጓል ሲሉ በፍኖት…
Read the full story at zena24now ↗