ሁለት የኢህአፓ አባላትን እና የፓርቲው ጠበቃ “የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል” በሚል ተከሰሱ
ሁለት የኢህአፓ አባላትን እና የፓርቲው ጠበቃ “የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል” በሚል ተከሰሱ ከትላንት በስቲያ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሁለት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) አባላት እና የፓርቲው ጠበቃ፤ “የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል” የሚል ውንጀላ ቀረበባቸው። ፖለቲከኞቹ እና ጠበቃው ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት (ህወሓት)፣ “ከሌሎች ጸረ- ሰላም ኃይሎች” እና “ጽምዶ” ተብሎ ከሚጠራው ኃይል ጋር “በመቀናጀት” በአዲስ አበባ ከተማ አባላትን “በመመልመል” እና “በማደራጀት” ተጠርጥረዋል። የፌደራል ፖሊስ እነዚህን ውንጀላዎች ያቀረበው፤ በአቶ አበበ አካሉ፣ አቶ ይስሀቅ ወልዳይ እና አቶ አበራ ንጉስ ላይ ነው። የኢሕአፓ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ይስሀቅ እና የህግ ባለሙያው አቶ አበራ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት፤ ከትላንት በስቲያ ሰኞ ሐምሌ 27…
Read the full story at zena24now ↗