በትግራይ በዘውዱ ሀፍቱ ግድያ እድሜ ልክ ተፈርዶባቸው የነበሩ ግለሰቦች ከእስር መፈታታቸውን 'ይኾኖ' ማህበር አስታወቀ
በትግራይ በዘውዱ ሀፍቱ ግድያ እድሜ ልክ ተፈርዶባቸው የነበሩ ግለሰቦች ከእስር መፈታታቸውን 'ይኾኖ' ማህበር አስታወቀ በትግራይ ክልል ወጣት ዘውዱ ሀፍቱን በመግደል ወንጀል በእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው የነበሩት ያሬድ ገብረሥላሴ እና አንገሶም ኃይለማርያም ከእስር መፈታታቸውን በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅት 'ይኾኖ' (Yikhono) አስታወቀ። እንደ ማህበሩ ገለፃ፣ ሁለቱ ግለሰቦች በፈጸሙት ዘግናኝ የግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተው የጽኑ እስራት ውሳኔ ከተላለፈባቸው ገና አንድ ወር ያህል እንኳ ሳይሞላው ነው ከእስር ነፃ የወጡት። ዕድሜዋ 32 የነበረችው ዘውዱ ሀፍቱ፣ ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በታቀደ ጥቃት በህዝብ ፊት በደረሰባት ከፍተኛ ድብደባ እና በመኪና በመጨፈለቋ ህይወቷ ማለፉ ይታወሳል። ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ በቆየባቸው ሁለት…
Read the full story at zena24now ↗