የሀላባ ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል የ903 ዜጎችን የዓይን ብርሃን መመለሱን አስታወቀ
የሀላባ ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል የ903 ዜጎችን የዓይን ብርሃን መመለሱን አስታወቀ በሀላባ ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል ለተከታታይ ዘጠኝ ቀናት ሲሰጥ በቆየዉ የነፃ የዓይን ምርመራና ህክምና የ903 ዜጎችን የአይን ብርሃን በመመለስ ተጠናቋል ። ሆስፒታሉ በሀላባ ዞን ከዉሃ አቅርቦት ችግር ጋር ተያይዞ የሚስተዋለዉን ሰፊ የዓይን ጤና ችግር ለመቅረፍ ከዳይሬክት ኤይድ ኢትዮጵያ ፣ከዘንባባ ጠቅላላ ሆስፒታል እና ከዞኑ ጤና መምሪያ ጋር በመተባበር ህክምናዉን ሲሰጥ መቆየቱን የሆስፒታሉ ምክትል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር መለሰ ሙዳ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ። በዚህም ከ1 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ነፃ የአይን ምርመራ አገልግሎት ማግኘታቸዉ የተገለፀ ሲሆን የአይን ሽፋሽፍት ችግርን ጨምሮ ሌሎች ዉስብስብ ችግር ላለባቸዉ ዜጎች ተጨማሪ ቀዶ ህክምና መደረጉ ተጠቁሟል ። ይህ የነፃ ህክምና አገልግሎት…
Read the full story at zena24now ↗