የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ኡባህ አደም (ዶ/ር) ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።

TIKVAHUNIVERSITYneutral2026-08-05 19:14:01 UTC
AdYour ad here[email protected]

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ኡባህ አደም (ዶ/ር) ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል። ፕሬዝዳንቷ፣ ዩኒቨርሲቲውን ከነበረበት ውስጣዊ ችግርና የሰላም እጦት ወዳለቀ ተቋማዊ ለውጥ በማሻገራቸው፣ በመማር ማስተማር፣ በምርምር እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎች ቀዳሚ ተቋም እንዲሆን ላደረጉት የመሪነት አበርክቶ ዕውቅናው እንደተሰጣቸው ተገልጿል። ሴት መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞችን ወደ አመራርነት እንዲመጡ በማገዝ እንዲሁም የሴቶችን የትምህርት አቅም እንዲሻሻል በማስቻል ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሴት ምሑራን እና ተመራማሪዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ ሴት ተመራማሪዎች ማኅበር ዕውቅና ሰጥቷቸዋል፡፡ ኡባህ አደም (ዶ/ር) ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ የድሬዳዋ ፕሬዝዳንት በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛሉ። @tikvahuniversity

Read the full story at tikvahuniversity ↗
AdYour ad here[email protected]