የመብራት ፖል የገጩ አሽከርካሪዎች ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ የካሳ ክፍያ ከፍለዋል ተባለ።
የመብራት ፖል የገጩ አሽከርካሪዎች ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ የካሳ ክፍያ ከፍለዋል ተባለ። በበጀት ዓመቱ በአዲስ አበባ ከተማ በከፍተኛ ወጪ የተገነቡ የመብራት ምሰሶዎችን ጥንቃቄ በጎደለው ማሽከርከር ከገጩ አሽከርካሪዎች የካሳ ክፍያ 9 ነጥብ 05 ሚሊዮን ብር ገቢ መገኘቱ ተገልጿል። ይህንን የገለጸው ከተቋቋመ ሁለት አመት ያልሞላው የአዲስ አበባ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ነው። የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሰብስብ ሁሴን (ዶ/ር ) በ2018 በጀት አመት በአዲስ አበባ የሚገኙ 41 ሺህ 283 የመብራት ምሰሶዎች መረጃ በጂኦግራፊያዊ መረጃ ስርዓት (GIS ) እንዲደራጁ መደረጉን ገልጸዋል። ባለሥልጣኑ "ዘመናዊ መብራት ለብሩህ አዲስ አበባ" የሚል ራዕይ ሰንቆ እየሰራ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በከተማዋ እየለሙ ያሉ ዘመናዊ የመብራት መሰረተ ልማቶችን ሁሉም ህብረተሰብ…
Read the full story at tikvahethmagazine ↗