" ለእኛ ሁለተኛ ሞት ነው። አዲስ ሀዘን ነው የሆነብን ! " - የዘውዱ ሃፍቱ እህት
" ለእኛ ሁለተኛ ሞት ነው። አዲስ ሀዘን ነው የሆነብን ! " - የዘውዱ ሃፍቱ እህት ከሁለት ዓመት በፊት በመቐለ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ በነበረችው ዘውዱ ሃፍቱ ግድያ ተጠርጥረው እድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸው ሁለት ፍርደኞች በነጻ እንዲሰናበቱ መወሰኑን ቢቢሲ አማርኛ የሟች ቤተሰብን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። የመቐለ መካከለኛ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ ያሬድ ገብረስላሴ እና አንገሶም ኃይለማርያምን " ነጻ ናቸው " ብሏቸዋል። ውሳኔው የተላለፈው ለታችኛው ፍርድ ቤት በማስረጃነት ቀርቦ የነበረ ዲጅታል ሰነድ ከፍርድ ቤቱ መዝገብ ቤት በመጥፋቱ መሆኑን የዘውዱ ቤተሰቦች ተናግረዋል። ይህ ወሳኝ ዲጅታል ማስረጃ ያሬድ የተባለው ፍርደኛ ይዞት ከነበረው ሲም ካርድ ጋር የተያያዘ ነው። ዘውዱ ነሃሴ 13/2015 የአሸንዳ በዓል ለመታደም ተዘጋጅታና የጓደኛዋን ልደት ለማክበር ከቤት በወጣችበት ' አዲሃውሲ…
Read the full story at tikvahethiopia ↗