መረጃ‼️
መረጃ‼️ ኢትዮጵያ በናይል ወንዝ ላይ አዲስ ግድብ እንድትገነባ ግብጽ አትፈቅድም ሲሉ የአገሪቱ የመስኖ ሚንስትር ሃኒ ስዊላም ትናንት ካይሮ ውስጥ በሠጡት መግለጫ ላይ ተናገሩ። ኢትዮጵያ በናይል ወንዝ ላይ አዳዲስ ግድቦችን የመገንባት ዕቅድ እንዳላት ይታወቃል ያሉት ስዊላም፣ ኾኖም ግብጽ ይህን ትፈቅዳለች ወይ ቢባል፣ 'መልሱ አትፈቅድም' የሚል ነው ማለታቸውን የአገሪቱ ጋዜጦች ጽፈዋል። ኢትዮጵያ ከሕዳሴ ግድብ ምን ያህል ውሃ በየጊዜው እንደምትለቅ አለማሳወቋ ሱዳንን "አስቸጋሪ ኹኔታ" ላይ ጥሏታል በማለት ስዊላም ኢትዮጵያን ወቅሠዋል ተብሏል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Read the full story at addis_reporter ↗