"...ጉልበት ሊያሳዩን አይደለም"!!
"...ጉልበት ሊያሳዩን አይደለም"!! "…በአዳራሹ ውስጥ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች አሉ::የከተማችን ከንቲባ ሙሉ ቀን እዚህ ይገኛሉ:: እና ሌሎችም የፌደራል አመራር ሚኒስትሮቹም እዚህ እንደሚገኙ አስተውላችኋል:: እዚህ የሚመጡ የክልል ርዕሳነ መስተዳድርም ሆኑ ከንቲባዎች እንዲሁም ሚኒስትሮች እንደሌላው ተማካሪ በትክክል ቁጭ ብለው በስነ ስርዓት እንዲማከሩ ነው እንጂ፤ የነሱን ስልጣን ወይም ጉልበት ሊያሳዩን አይደለም::" ይህንን የተናገሩት የሀገራዊ ምክክሩ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን ዓርዓያ ናቸው። ትናንት ከቀኑ 9:00 ሰዓት በተሰጠው መግለጫ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በንዑሳን ቡድኖች የቀረቡ ሀሳቦችን የማደራጀትና የማስተካከል ስራ ባለመጠናቀቁ የ500 ሰዎች ትልቁ ጉባዔ መጀመር መዘገየቱን አስታውቋል። ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን ዓርዓያ እንደገለጹት፣ ቀደም ሲል ሰኞ…
Read the full story at wasulife ↗