#AAU
#AAU አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ወደ ተቋሙ አዲስ ለሚገቡ ተማሪዎች የመረጃ ሳምንት አዘጋጅቷል፡፡ በዩኒቨርሲቲው ዋናው ጊቢ፣ ፎረም ሕንፃ ከነሐሴ 08-16/2018 በሚቆየው የመረጃ ሳምንት፣ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተለያዩ አካዳሚክ እና ተቋማዊ መረጃዎችን ከዩኒቨርሲቲው የሚያገኙ ይሆናል፡፡ በፕሮግራሙ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ስለ መግቢያ መስፈርቶች፣ የማመልከቻ ሂደቶች፣ የመጀመሪያ ዲግሪ የመግቢያ ፈተና (UAT)፣ በዩኒቨርሲቲው ስለሚሰጡ የስኮላርሺፕ አማራጮች (በመንግሥት፣ በግል እና ፕሬዝዳንታዊ) እንዲሁም ስለ ምደባ መረጃ ያገኙበታል፡፡ @tikvahuniversity
Read the full story at tikvahuniversity ↗