እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ነገር ሁሉ ትከልለን፤ ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን🙏

ADDIS_NEWSneutral2026-08-06 13:49:27 UTC
AdYour ad here[email protected]

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ነገር ሁሉ ትከልለን፤ ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን🙏 ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ በትንቢቱ ኢሳ 7፡14 "ድንግል ትጸንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች" ብሎ የተናገረላት ያቺ ድንግል በዚህች ዕለት ተወለደች፡፡ ይህች ቀን ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት በመዝ 44÷9 "የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች" ብሎ የተናገረላት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተገኘችባት ናት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም በራዕይ 12÷1 "ፀሐይን የተጎናጸፈች፣ ጨረቃን የተጫማች፣ አስራ ሁለት የክዋክብት አክሊል በራሷ ላይ ያላት" ብሎ የመሰከረላት የብርሃን እናቱ ድንግል ማርያም የተወለደችባት ቀን ናት፡፡ የእርስዋም ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ ድንገት የተከሰተ ሳይሆን አስቀድሞ በትንቢት፣ በምሳሌና በራዕይ የሰውን ልጅ ድኅነት በጉጉት ሲጠባበቁ…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]