የሻደይ በዓልን ከሰቆጣ ባሻገር በአዲስ አበባ ከተማ ለማክበር ዝግጅት መደረጉ ተነገረ

ZENA24NOWneutral2026-08-07 10:30:23 UTC
AdYour ad here[email protected]

የሻደይ በዓልን ከሰቆጣ ባሻገር በአዲስ አበባ ከተማ ለማክበር ዝግጅት መደረጉ ተነገረ የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ባሕል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ይርጋ ማርዬ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት የዘንድሮውን የሻደይ በአል ከሰቆጣ ባሻገር በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ተደርጓል። በአሉን በተሳካ መልኩ ለማክበር ኮሚቴ እንዲቋቋም መደረጉን ገልፀዋል። በዓሉ የልጃገረዶች የሕፃናትና የእናቶች ነው ያሉት ኃላፊው እነዚህን አካላት ታሣቢ ያደረገ በጎጥ፣ በደብር፣ ቤት ለቤትና በዐደባባይ ለማክበር ታስቦ እቅድ መውረዱን ተናግረዋል። በዞን ደረጃ ከነሐሴ 15 እስከ 18 ቀን ድረስ በሰቆጣ ከተማ እንደሚከበር አስረድተዋል።ይህ በአል በሰቆጣ ከተማ ከተከበረ በኋላ በቀጣዮቹ ቀናት በአዲስ አበባ እና በባሕር ዳር ከተማ ጭምር ለማክበር ታቅዷል። በዓሉ ሲከበር የብሔረሰቡን…

Read the full story at zena24now ↗
AdYour ad here[email protected]