የየመን ሁቲዎች ጥቃት

ADDIS_NEWSneutral2026-08-07 13:21:02 UTC
AdYour ad here[email protected]

የየመን ሁቲዎች ጥቃት የየመን ሁቲዎች በሳውዲ ዐረቢያ በሚደገፈው የየመን መንግስት ኃይሎች ላይ ባደረሱት ጥቃት በትንሹ የ58 ሰዎች ህይወት ተቀጠፈ። ጥቃቱ በሰው አልባ አውሮፕላን እና ሚሳዔል የተፈፀመ መሆኑንም ወታደራዊ ምንጮች ይፋ አድርገዋል። ጥቃቱ በሀገሪቱ የእርስበርስ ግጭት ከተቀሰቀሰ ወዲህ እጅጉን አስከፊ ከሚባሉት ክስተቶች መካከል የሚመዘገብ ሆኗል። ሁቲዎች በሳውዲ ዐረቢያ ላይ እና በመንግስታቱ ድርጅት እውቅና የተሰጠውን የየመን መንግስት ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ማጥቃት ቀጥለዋል። ሪያድ ድጋፍ በማድረግ ወታደራዊ አቅሙን የኤደኑ መንግስት እያጠናከረ ነው የሚል አረዳድ ያላቸው አንሳራአላሆች ድሮንና ሚሳዔልን በመጠቀም ወታደራዊ ዒላማዎችን አውድመናል ብለዋል። @Addis_News @Addis_News

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]