በአዲግራት ከተማ ደረጃውን ያልጠበቀ የአልኮል መጠጥ ሲያሰራጩ የነበሩ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ።
በአዲግራት ከተማ ደረጃውን ያልጠበቀ የአልኮል መጠጥ ሲያሰራጩ የነበሩ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ። የዓዲግራት ከተማ ፍርድ ቤት ደረጃውን ያልጠበቀና ፈቃድ ሳይኖረው የታሸገ የአልኮል መጠጥ (አረቄ) ለህብረተሰቡ ሲያሰራጩ የነበሩ ሦስት ግለሰቦች እያንዳንዳቸው በ8 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እና በ25 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ መወሰኑን ብስራት ከአዲግራት ከተማ የኮሚኒኬሽን ፅሕፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያሳያል። ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ጥፋተኛ ተብለው የተፈረደባቸው ግለሰቦች የዓዲግራት ከተማ ነዋሪ የሆኑት አንደኛ ተከሳሽ ኢንጂነር ዑቅባይ በርሀ ይፍጠር፣ ሁለተኛ ተከሳሽ ፅዱቅ በርሀ ይፍጠር እና ሦስተኛ ተከሳሽ ሊቀ ሁሩያን ጋይም አስገለ አለማየሁ ናቸው። ተከሳሾቹ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም በመኖሪያ ቤት ውስጥ አረቄ በማዘጋጀትና የተለያዩ ስቲከሮችን በመጠቀም…
Read the full story at addis_reporter ↗