የአንስቴዥያ ሙያ የተግባር ፈተና ተመዛኞች ውጤት!

TIKVAHUNIVERSITYneutral2026-08-07 15:05:34 UTC
AdYour ad here[email protected]

የአንስቴዥያ ሙያ የተግባር ፈተና ተመዛኞች ውጤት! ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም በጤና ሚኒስቴር የተሰጠውን የተግባር ፈተና የወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች ውጤታችሁን ማየት ትችላላችሁ። https://hple.moh.gov.et ላይ በመግባት የብሔራዊ መለያ ቁጥር (FAN) እና Password በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል። በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ከዛሬ ነሐሴ 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት በነጻ ስልክ ቁጥር 952 በመደወል ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት እና የተማራችሁበትን የትምህርት ተቋም ስም በመግለፅ ቅሬታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ ተብሏል። @tikvahuniversity

Read the full story at tikvahuniversity ↗
AdYour ad here[email protected]