ኢትዮጵያ በውድድሩ የመጀመሪያዋን ወርቅ አግኝታለች።

AMHARAMASSMEDIAneutral2026-08-08 07:19:43 UTC
AdYour ad here[email protected]

ኢትዮጵያ በውድድሩ የመጀመሪያዋን ወርቅ አግኝታለች። ኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የዓለም ሻምፒዮና የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስመዘገበች። በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ ባለው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና፤ በሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድር ኢትዮጵያ የወርቅና ብርና ሜዳሊያ አግኝታለች። አትሌት አልማዝ ዮሃንስ ርቀቱን በ9:15.81 በሆነ ጊዜ ቀዳሚ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች። አትሌት ወሰኔ አሰፋ ደግሞ 9:30.50 በሆነ ጊዜ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የብር ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች። ኢትዮጵያ እስካሁን በውድድሩ አንድ የወርቅ ፣ ሁለት የብር እና አንድ የነሀስ ሜዳልያ አግኝታለች። #አሚኮ #Ethiopia #WirldAthletics

Read the full story at amharamassmedia ↗
AdYour ad here[email protected]