ማን ከእኔ በፊት ሀገሬ ይበል? - የዘመናት ቋጠሮን ፈትቶ ኢትዮጵያን በልጆቿ ፍቅር የማነጽ ታሪካዊ ጥሪ
ማን ከእኔ በፊት ሀገሬ ይበል? - የዘመናት ቋጠሮን ፈትቶ ኢትዮጵያን በልጆቿ ፍቅር የማነጽ ታሪካዊ ጥሪ ኢትዮጵያ የረጅም ዘመናት ታሪክ እና የደማቅ ባሕል ባለቤት ብትኾንም የዘመናት ታሪኳ ግን በደም እና በእንባ የተጻፉ በርካታ አሳዛኝ ምዕራፎችን አልፏል። "ማን ከእኔ በፊት ሀገሬ ይበል?" የሚለው ጥያቄ የዛሬዋን ኢትዮጵያ ህልውና የሚፈትን እያንዳንዱ ዜጋ የልቦናውን ጓዳ ፈትሾ ሊመልሰው የሚገባ የዘመናችን አንገብጋቢ የህሊና ጥሪ ነው። ለዓመታት እኔነት ከእኛነት በልጦ የፖለቲካ ልሂቃን ሽኩቻ፣ የታሪክ ትርክቶች ግጭት እና የመጠላለፍ ፖለቲካ ሀገሪቱን ወደ ጥፋት አዘቅት ውስጥ ሲከታት ቆይቷል። ይህ የተንዛዛ የግጭት አዙሪት የዜጎችን ሕይወት ከመቅጠፉም በላይ ማኅበራዊ ትስስርን አላልቷል፤ ኢኮኖሚን አሽመድምዷል፤ ሀገሪቱን የውክልና ጦርነት እና የድህነት መጫወቻ እንድትኾን አድርጓታል።…
Read the full story at amharamassmedia ↗