በአለታ ወንዶ ከተማ ትናንት ምሽት በደረሱ ሁለት የተሽከርካሪ አደጋዎች የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በአለታ ወንዶ ከተማ ትናንት ምሽት በደረሱ ሁለት የተሽከርካሪ አደጋዎች የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ 👉 ከማቾቹ ስድስቱ ሰዎች የፌዴራል ፖሊስ አባላት ናቸው በሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ እንዳስታወቀው አደጋዎቹ ትናንት ምሽቱ የደረሱት በከተማው ቡልቱማ በተባለ ቀበሌ ውስጥ ነው ፡፡ አደጋው የደረሰው ከቦረና አቅጣጫ ወደ ሀዋሳ ሲጓዝ የነበረና የመለያ ኮዱ 1190 የሆነ የፌዴራል ፖሊስ ተሽከርካሪ በቀበሌው ሲደርስ በመገልበጡ ነው ፡፡ በአደጋው የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉን በመምሪያው የትራፊክ አደጋ መከላከልና ምርመራ የሥራ ሂደት ኃላፊ ኢንስፔክተር መለሰ ቡኑራ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል ፡፡ በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት ስድስቱ ሰዎች በተሽከርካሪው ተሳፍረው የነበሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት መሆናቸውን ኢንስፔክተር መለሰ ገልጸዋል። በተጨማሪም በዚሁ ቀበሌ ሌላ ሲኖትራክ የጭነት ተሽከርካሪ…
Read the full story at zena24now ↗