ኬንያ ወደ ሀገሯ ለሚገቡ የውጭ ዜጎች የጤና ኢንሹራንስ ግዴታ አደረገች
ኬንያ ወደ ሀገሯ ለሚገቡ የውጭ ዜጎች የጤና ኢንሹራንስ ግዴታ አደረገች የኬንያ ጤና ሚኒስቴር ከኬንያ ውጭ የሚመጡ ማንኛውም ሀገር ዜጎች ወደ ሀገሪቱ ከመግባታቸው በፊት ሕጋዊ የጉዞ ጤና ኢንሹራንስ ሊኖራቸው እንደሚገባ የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ አወጣ። በካቢኔ ሴክሬታሪ አደን ዱአሌ በተፈረመው በዚህ ይፋዊ ሰነድ መሠረት፣ የኬንያ ዜጋ ያልሆኑ እና ለተለያዩ ጉዳዮች ከ12 ወራት ላነሰ ጊዜ ወደ ኬንያ የሚገቡ የትኛውንም ሀገር ጎብኚዎችና መንገደኞች ይህ መመሪያ ይመለከታቸዋል ተብሏል። መንገደኞች ከገዛ ሀገራቸው የገዙት የጉዞ ጤና ኢንሹራንስ በኬንያ መንግሥት የወጣውን የመድህን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ፣ በኬንያ የኤሌክትሮኒክ የጉዞ ፈቃድ (eTA) ስርዓት ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል። ከጉዞ በፊት ኢንሹራንስ ያልያዙ መንገደኞች ደግሞ ኬንያ አየር መንገድ ወይም የድንበር በር ሲደርሱ በኬንያ…
Read the full story at addis_news ↗