አሚኮ ማኅበራዊ ኀላፊነቱን በመወጣት ተተኪ ትውልድ ላይ በትኩረት እየሠራ ይገኛል።
አሚኮ ማኅበራዊ ኀላፊነቱን በመወጣት ተተኪ ትውልድ ላይ በትኩረት እየሠራ ይገኛል። የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) መረጃን በልዩ ልዩ አማራጮች ከማሰራጨት ባሻገር በተግባር የተደገፈ ማኅበራዊ ኀላፊነቱን በመወጣት ተተኪ ትውልድን የመቅረጽ እና የመደገፍ ሥራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። የዚሁ በጎ አድራጎት አካል የኾነው የአሚኮ አዲስ አበባ ዘርፍ መሪዎች እና ሠራተኞች በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኘው ወጋገን 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ስጦታ አበርክተዋል። የኮርፖሬሽኑ የአዲስ አበባ ዘርፍ የንግድ ሥራዎች ዳይሬክተር ታደለ ፋንታሁን እንደገለጹት ተቋሙ ከተለመደው የሚዲያ ሥራው ጎን ለጎን በደም ልገሳ፣ በአረጋውያን ቤት እድሳት፣ አቅመ-ደካሞችን እና ወላጅ አልባ ሕጻናትን በቋሚነት በመደገፍ አርዓያነት ያለው ተግባር እያከናወነ ይገኛል ነው ያሉት።…
Read the full story at amharamassmedia ↗