የምክክሩ የአጀንዳ ምክረ ሃሳቦች ለሥራ ቡድኖች መቅረብ ጀመሩ
የምክክሩ የአጀንዳ ምክረ ሃሳቦች ለሥራ ቡድኖች መቅረብ ጀመሩ የምክክሩ የአጀንዳ ምክረ ሃሳቦች ለሥራ ቡድኖች መቅረብ መጀመራቸው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ከእያንዳንዱ የባለ 500 አባላት የሥራ ቡድን የተመረጡ 30 አባላት ከስልታዊ ቡድኖች የቀረቡ የአጀንዳ ምክረ ሃሳቦችን ተቀናጅተው 500 አባላት ላሏቸው 8 የሥራ ቡድኖች ማቅረብ ጀምረዋል፡፡ የተጠናቀሩ የአጀንዳ ሃሳቦች ላይ የመወያየቱ ሒደት በመጪው ሰኞ የሚቀጥል መሆኑንም ኮሚሽኑ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡ ይህ የምክክር ደረጃ አንድ አጀንዳ ላይ የሚወያዩ 500 ተመካካሪዎች በሚወያዩበት አጀንዳ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ የመጨረሻ ምክረ ሃሳብ ለማቅረብ ሞቅ ያለ ውይይት የሚያደርጉበት መሆኑ ተመልክቷል። @Addis_News @Addis_News
Read the full story at addis_news ↗