በአለታ ወንዶ በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት በደረሱ ሁለት አደጋዎች የ7 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-08-08 19:42:11 UTC
AdYour ad here[email protected]

በአለታ ወንዶ በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት በደረሱ ሁለት አደጋዎች የ7 ሰዎች ሕይወት አልፏል። በደቡባዊ ሲዳማ ዞን አለታ ወንዶ ቡልቱማ ኦሊራ ቀበሌ፣ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ከምሽቱ 2፡30 ገደማ በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት በደረሱ ሁለት የትራፊክ አደጋዎች 7 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ከቦረና ወደ ሀዋሳ 13 የፌዴራል ፖሊስ አባላትን ይዞ ሲጓዝ የነበረ ሰሌዳ ቁጥሩ EFP 1190 የሆነ ኦራል ተሽከርካሪ መንገድ ስቶ በመገልበጡ 6 የፖሊስ አባላት ሲሞቱ፣ በሌላኛው አደጋ ሲኖትራክ ከአይሱዙ ጋር ተጋጭቶ የመኖሪያ ቤትን ደርምሶ በመግባቱ አንድ እግረኛ ሕይወቱን አጥቷል። በአደጋዎቹ የተጎዱ ሰዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ሕክምና ላይ ሲሆኑ፣ በሰውና በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የሲዳማ ክልል ፖሊስ ገልጿል። (ሲዳማ ፖሊስ) @tikvahethiopia

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]