#Senegal🇸🇳

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-08-08 22:27:44 UTC
AdYour ad here[email protected]

#Senegal🇸🇳 ሴኔጋል ከወራት በፊት በግብረሰዶማዊነት ላይ ያወጣችውን ጥብቅ ሕግ በማስፈጸም 71 ወንዶችን " ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ ድርጊት " በሚል እንዲታሰሩ አድርጋ ወደ ፍርድ ቤት አቅርባለች። በቅርብ ወራት ብቻ ከ100 በላይ ሰዎች በተመሳሳይ የግብረሰዶማዊነት ጉዳይ ተጠርጥረው መያዛቸው ተገልጿል። ከነዚህም ውስጥ የሀገሪቱ ታዋቂ ሰዎች አሉበት ተብሏል። በሴኔጋል ባለፈው መጋቢት ወር የተሻሻለው ጥብቅ ሕግ ግብረሰዶማዊ ግንኙነት እስከ 10 ዓመት ዘብጥያ ያስወረውራል። ከእስር በተጨማሪ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት አለው። ግብረ ሰዶማዊነትን የሚያስተዋውቁ ወይም የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉ ግለሰቦች ከ3 እስከ 7 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ ሕጉ ይፈቅዳል። አፀያፊ የተባለውን ይህን ድርጊት የሚያበረታታ ማንኛውም ድርጊት እንደ ወንጀል እንዲታይ ተደርጓል። ነሐሴ 2 ቀን 2018 ዓ/ም…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]