"ታጣቂዎች ከውጭ ኃይሎች ጋር በመሻረክ 'ያልተቀደሰ ጋብቻ' ፈጥረዋል" አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

ZENA24NOWneutral2026-08-09 09:35:33 UTC
AdYour ad here[email protected]

"ታጣቂዎች ከውጭ ኃይሎች ጋር በመሻረክ 'ያልተቀደሰ ጋብቻ' ፈጥረዋል" አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) በኦሮሚያ፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች መንግሥትን ማሸነፍ እንደማይችሉ ሲረዱ "ያልተቀደሰ ጋብቻ" መፍጠራቸውን ገለጹ። ታጣቂዎቹ ኤርትራን እና ሱዳንን ጨምሮ ከውጭ ተዋናዮች ድጋፍ ለማግኘት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ሕዝቡ በጥንቃቄ ሊረዳው እንደሚገባ ያስገነዘቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ቀደም ሲል ሀገሪቱን በብቸኝነት ይመራ የነበረው ቡድን ያጣውን ሥልጣን በኃይል ለመመለስ ማሰቡ ለሀገሪቱ ግጭቶች መንስኤ መሆኑን ገልጸዋል። #ዳጉ_ጆርናል

Read the full story at zena24now ↗
AdYour ad here[email protected]