"የታጠቁ ኃይሎች መንግሥትን ማሸነፍ ባለመቻላቸው ያልተቀደሰ ጋብቻ ፈጥረዋል" — ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ

WASULIFEneutral2026-08-09 10:02:43 UTC
AdYour ad here[email protected]

"የታጠቁ ኃይሎች መንግሥትን ማሸነፍ ባለመቻላቸው ያልተቀደሰ ጋብቻ ፈጥረዋል" — ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በአማራ፣ በኦሮሚያና በትግራይ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች መንግሥትን ማሸነፍ እንደማይችሉ ሲረዱ "ያልተቀደሰ ጋብቻ" መፍጠራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፋና ጋር በኦሮምኛ በነበራቸው ቆይታ አክለውም፣ እነዚህ ኃይሎች ቀደም ሲል እርስ በእርስ ሲወጋገዙ የነበሩ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን ተስፋ በመቁረጥና በመዳከማቸው ምክንያት በአንድ ላይ መሰለፋቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም የታጠቁት ቡድኖች እንደ ኤርትራና ሱዳን ካሉ የውጭ አካላት እርዳታ በመጠየቅ ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው፣ በጫካ የሚገኘው የሸኔ ቡድንም ግልጽ ዓላማና ግብ የሌለው፣ ለውጭ አካላት የሚሠራ ተቀጣሪ ኃይል መሆኑን ሕዝቡ ሊገነዘበው እንደሚገባ አስገንዝበዋል።…

Read the full story at wasulife ↗
AdYour ad here[email protected]