በታሪክ በኑክሌር ቦምብ የተመታች የመጨረሻዋ ከተማ 81ኛ ዓመቷን ዘክራለች

TIKVAHETHMAGAZINEneutral2026-08-09 13:47:55 UTC
AdYour ad here[email protected]

በታሪክ በኑክሌር ቦምብ የተመታች የመጨረሻዋ ከተማ 81ኛ ዓመቷን ዘክራለች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማጠቃለያ ላይ አሜሪካ በጃፓኗ ናጋሳኪ ከተማ ላይ ያደረሰችውን የአቶሚክ ቦምብ ድብደባ 81ኛ ዓመት ከ90 በላይ ሀገራት ተወካዮች በተሳተፉበት የመታሰቢያ መርሐግብር ተከናውኗል። በዕለቱ እ.ኤ.አ ነሐሴ 9 ቀን 1945 "ፋት ማን" የተሰኘው የፕሉቶኒየም ቦምብ በከተማዋ ላይ ፈንድቶ ከፍተኛ እልቂት ያስከተለበትን ቅጽበት በማሰብ የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት ተደርጓል። ከጥቃቱ ሶስት ቀናት ቀደም ብሎ በሂሮሺማ ከተማ ላይ በተጣለው ቦምብ ወደ 140 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ያለቁ ሲሆን፣ በናጋሳኪ በደረሰው ጥቃት ደግሞ በጥቃቱ ቅጽበት እና በቀጣዮቹ ወራት ውስጥ ከ74 ሺህ በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ከፍንዳታው የተረፉትና "ሂባኩሻ" በመባል የሚታወቁት የከተማዋ ነዋሪዎችም ለበርካታ ዓመታት…

Read the full story at tikvahethmagazine ↗
AdYour ad here[email protected]