ከጥቅምት 30 ጀምሮ የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ እንደሚከፈል የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር አሳወቀ።

NATNAELMEKONNEN21neutral2026-11-02 12:40:14 UTC
AdYour ad here[email protected]

ከጥቅምት 30 ጀምሮ የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ እንደሚከፈል የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር አሳወቀ። የትግራይ ባለአደራ አስተዳደር የኢኮኖሚ እና መልሶ ግንባታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቴዎድሮስ አረጋይ (ዶ/ር)፤ የደመወዝ ክፍያውን ለማስፈጸም የፋይናንስ ዝግጅቶች መደረጋቸውን ለኤፍኤምሲ ገልጸዋል። በሥራ ቦታቸው ተገኝተው ሥራ መጀመራቸውን ሪፖርት ላደረጉና በሕጋዊ ሁኔታ በመንግሥት ተቋማት ተቀጥረው ለሚሠሩ ሠራተኞች ከጥቅምት 30/2019 ዓ/ም ጀምሮ ደመወዝ እንደሚከፈል አስረድተዋል። " የደመወዝ ክፍያው መጀመር በክልሉ የመንግሥት ተቋማት ሥራ መልሶ ለማስጀመርና የሠራተኞችን የሥራ ተነሳሽነት ለማጠናከር ከሚደረጉ ጥረቶች አንዱ ነው " ብለዋል። በትግራይ ሠራተኞች የወራት ደመወዝ ባለመከፈሉ ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ለከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስና ችግር መዳረጋቸው በተደጋጋሚ መነገሩ ይታወሳል።…

Read the full story at natnaelmekonnen21 ↗
AdYour ad here[email protected]