ባለቤቱን በመግደል የተከሰሰው ግለሰብ በ21 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ።
ባለቤቱን በመግደል የተከሰሰው ግለሰብ በ21 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ። በአዲግራት ከተማ ቀበሌ 06 ዞን 6 ነዋሪ የሆነው አቶ ሳምሶም ሓጎስ አብርሃ የተባለው ተከሳሽ የሁለት ልጆቹ እናት የሆነችውን የ22 ዓመቷን ባለቤቱን ወይዘሮ ቅሳነት ተሾመን መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በፈፀመው አሰቃቂ የነፍስ ግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ነው በ21 አመት ከ 3 ወር ፅኑ እስራት የተቀጣው። የምስራቅ ትግራይ ዞን ዓቃቤ ሕግ አቶ መሓሪ እንደገለፁት ተከሳሹ በከባድ የነፍስ ግድያ ወንጀል ተከሰሶ ጥፋተኛነቱ ከተረጋገጠ በኋላ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ከዚህ ቀደም ወንጀል ፈፅሞ የማያውቅ እና ቤተሰብ አስተዳዳሪ የነበረ መሆኑን እንደ ማቅለያ እንዲሁም ሁለት የማክበጃ ነጥቦችን በመያዝ ሕግን መሰረት ያደረገ ውሳኔ ሰጥቷል ብለዋል። በአዲግራት ከተማ የሴቶች ማህበር ሊቀመንበር እና…
Read the full story at zena24now ↗