በራያ አላማጣ ወረዳ "የትግራይ ኃይሎችን ዒላማ ያደረገ" የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ምንጮች ተናገሩ!

ADDIS_NEWSneutral2026-08-11 11:11:47 UTC
AdYour ad here[email protected]

በራያ አላማጣ ወረዳ "የትግራይ ኃይሎችን ዒላማ ያደረገ" የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ምንጮች ተናገሩ! በትግራይ ክልል ራያ አላማጣ ወረዳ "መረዋ" የተባለ ቀበሌ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት የሰዎች ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ባለሥልጣን እና የትግራይ ኃይሎች ምንጮች ተናገሩ። "ትምህርት ቤት" ላይ ተፈጸመ በተባለው ጥቃት "ሦስት የትግራይ ኃይሎች አባላት ሲገደሉ፤ ሰባቱ መጎዳታቸውን" ምንጮቹ ለቢቢሲ ትግርኛ ገልጸዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሦስት ምንጮች እንደሚስረዱት፣ የድሮን ጥቃቱ የተፈጸመው ትናንት ሰኞ ነሐሴ 5/2018 ዓ.ም. ጠዋት 2፡30 ገደማ ነው። ከአላማጣ ከተማ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በዚህ ስፍራ ሦስት ጊዜ ጥቃት እንደደረሰ ተገልጿል።በጥቃቱ ዒላማ የተደረገው "አርሚ 26" የተባለው የትግራይ ኃይሎች አባላት እንደሆኑ ቢቢሲ ትግርኛ ከወታደራዊ አዛዦች እና ከደቡብ…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]