ግልገል በለስ‼️
ግልገል በለስ‼️ በጋራ ግልገል በለስ ከተማን ለመቆጣጠር ሞክረዋል - የመተከል ዞን አስተዳደር‼️ የመተከል ዞን አስተዳደር የፋኖ ሀይሎችና የጉሙዝ ሀይሎች ግልገል በለስ ከተማን ዛሬ ማለትም ነሐሴ 5/2018 ከንጋቱ 12:00 ሰዓት አካባቢ ለመቆጣጠር ሞክረው እንደነበረ ገለፀ። የዞኑ አስተዳደር ይሄ ኦፕሬሽን እንዳልተሳካና ከተማውም ወደ ቀድሞ ሰላሙ መመለሱን አስታውቋል። በከተማዋ ዋና መንገድ መድፍ ጭምር ሲንቀሳቀስ እንደነበር የከተማዋ ነዋሪዎች ለአዩዘሀበሻ የገለፁ ሲሆን ጠዋት አካባቢ በከተማ መናኸሪያ ውስጥ ፈንጂ በማፈንዳት በርካታ ተሳፋሪዎች እንደተጎዱ እና እንዲሁም 10 ሰዎች እንደሞቱ ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል። ተጎጂዎች ፓዊ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ገልፀውልናል። ምስል:- ከግልገል በለስ ከተማ(የመድፍ እንቅስቃሴ) @Addis_News @Addis_News
Read the full story at addis_news ↗