በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተለያዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡና በሳይንስ ትምህርቶች እና በፈጠራ ልዩ ተሰጥኦ ላላቸው 40 ተማሪዎች የተዘጋጀ ስልጠና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እየተሰጠ ነው፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተለያዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡና በሳይንስ ትምህርቶች እና በፈጠራ ልዩ ተሰጥኦ ላላቸው 40 ተማሪዎች የተዘጋጀ ስልጠና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እየተሰጠ ነው፡፡ ስልጠናው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት እንዲሁም ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው፡፡ ለ45 ቀናት የሚቆየው የንድፈ-ሐሳብ እና የተግባር ስልጠናው፤ በአስትሮኖሚ፣ በሮኬት ሳይንስ፣ በድሮን (UAV)፣ በጂአይኤስ እና በሳታላይት ሲስተም ላይ ትኩረተት ያደርጋል፡፡ ስልጠናው በክልሉ ባሉ አራቱም ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡ @tikvahuniversity
Read the full story at tikvahuniversity ↗