የፍትሕ ሚኒስቴር ተጥለው ለሚገኙ ሕፃናት ማቆያ ክፍል ውስጥ የሚውሉ ቁሳቁሶችን አበረከተ።
የፍትሕ ሚኒስቴር ተጥለው ለሚገኙ ሕፃናት ማቆያ ክፍል ውስጥ የሚውሉ ቁሳቁሶችን አበረከተ። የፍትሕ ሚኒስቴር ተጥለው ለሚገኙ ሕፃናት ማቆያ ክልል ውስጥ የሚውሉ የተለያዩ ቁሣቁሶችን ለኦሮሚያ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ማበርከቱ ተገልጿል ። የፍትሕ ሚኒስቴር የሴቶች እና ሕፃናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ዳግማዊት አለምነህ እንደገለፁት በተለያዩ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ውስጥ ተወልደው ለሚጣሉ ሕፃናት ጊዚያዊ ማቆያ የሚውሉ ቁሣቁሶችን መለገስ ያስፈለገበት ምክኒያት ችግሩ በአሁኑ ጊዜ ተበራክቶ በመገኘቱ እንደሆነ ገልፀዋል። ከጋብቻ ውጪ በአላስፈላጊ እርግዝና የሚወለዱ ሕፃናት ሕጋዊ ሒደቱን ተከትሎ ለአሣዳጊዎች እስኪተላለፉ ድረስ በፖሊስ ዘንድ የሚቆዩ በመሆኑ የተመጣጠነ ምግብ ፣ የጤና ክትትል እና ለንፅሕና መጠበቂያ የሚውሉ ቁሣቁሶች አስፈላጊ እንደመሆናቸው ሚኒስትሩ ይሕንን በመረዳት…
Read the full story at zena24now ↗