የሞራል ልዕልና! የአቶ ዶዮ ኡመር ዋሬ የሚያስመሰግን ተግባር
የሞራል ልዕልና! የአቶ ዶዮ ኡመር ዋሬ የሚያስመሰግን ተግባር አቶ ዶዮ ኡመር ዋሬ በአማራ ክልል ነዋሪና የሰላም አስከባሪ ሚሊሻ አባል ናቸው። ነሐሴ 04 ቀን 2018 ዓ.ም የዚያድ አብዱናስር ነጋዮ የተባለ ግለሰብ 900,000 ብር በስህተት ወደ አካውንታቸው በገባበት ወቅት፣ ገንዘቡ የእርሳቸው አለመሆኑን ተረድተው ሳይዘገዩ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰንበቴ ቅርንጫፍ በመሄድ ለባለቤቱ እንዲመለስ አድርገዋል። አቶ ዶዮ ይህንን ማድረጋቸው የሞራል ግዴታቸው እንደሆነ የገለጹ ሲሆን፣ የባንኩ ቅርንጫፍም ላሳዩት የላቀ የታማኝነት ተግባር የምስጋና ምስክር ወረቀት አበርክቶላቸዋል። Via -kalid oumer
Read the full story at brook_news_ethiopia ↗