በመተከል ዞን ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ከአስር በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ‼
በመተከል ዞን ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ከአስር በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ‼ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ዛሬ ማለዳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ከአስር በላይ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የአይን ምስክሮች ተናገሩ። በከተማዋ የአውቶቢስ መናኸሪያ አካባቢ በተፈጸመው ጥቃቱ በርካቶች ተጎድተው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የአይን ምስክሮቹ ተናግረዋል። የመተከል ዞንም በከተማዋ ጥቃት መፈጸሙን ዛሬ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ ባሠራጨው ማብራሪያ አረጋግጧል። ይሁንና በጥቃቱ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ስለደረሰው ጉዳት ያለው ነገር የለም። የአይን ምስክሮች እንደተናገሩት፤ ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ያደረሱት ተጓዦች ማለዳ ላይ አውቶቢስ ለመያዝ በተሰበሰቡበት ወቅት በከባድ መሳሪያ በመጠቀም እንደሆነ ለዶቸ ቬለ ተናግረዋል። @Addis_News @Addis_News
Read the full story at addis_news ↗