ሶስት አሠልጣኞችና አራት አትሌቶች አሜሪካ ፖርትላንድ ላይ ኮበለሉ!
ሶስት አሠልጣኞችና አራት አትሌቶች አሜሪካ ፖርትላንድ ላይ ኮበለሉ! 🔴 ቡድኑ በቺካጎ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ ሲመለስ 7 የቡድኑ አባላት ከልዑካን ቡድኑ ጋር የሉም 🔴 የአሜሪካኗ ዩጂን ኦሪገን ለኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ውጤት የሚመዘገብባት ከተማ ብቻ ሳትሆን በርካቶች የሚኮበልሉባት ታሪካዊ ከተማም ሆና ተመዝግባለች ✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት) በአሜሪካ ኦሪገን ዩጂን ሲካሄድ የነበረው ከ20 ዓመት በታች 21ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መጠናቀቁ ይታወሳል። ወደ ውድድሩ ስፍራ የተጓዘችው ሀገራችን ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው 2 ወርቅ፣3 ብር እና 1 ነሃስ በድምሩ 6 ሜዳሊያ ማግኘቷም ይታወቃል። ከወደ ኦሪገን ከደቂቃዎች በፊት የደረሠን አስደንጓጭ ዜና ለሻምፒዮናው ከተጓዙት የልዑኳን ቡድን አባላት መካከል ሰባቱ ፖሬትላንድ ላይ መኮብለላቸው ተረጋግጧል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ…
Read the full story at addis_reporter ↗