ኢትዮጵያን ከወጣቶቿ ነጥሎ ማየት አይቻልም!

ABIYAHMEDALIOFFICIALneutral2026-08-12 05:41:58 UTC
AdYour ad here[email protected]

ኢትዮጵያን ከወጣቶቿ ነጥሎ ማየት አይቻልም! ‎ የህዝባችን የእድሜ ስብጥር እንደሚያመላክተው ወጣቶች ከፍተኛውን ቁጥር መያዛቸው፣ ብልጽግናን ለማረጋገጥና ለማፅናትም ታላቅ እድል ነው። ‎ ‎የኢትዮጵያ ወጣት መልካም ዓላማን አንግቦ የሚንቀሳቀስ፣ የለውጥ ዋነኛ ሞተርና የሉዓላዊነታችን ጽኑ ማገር ነው! የኢትዮጵያ ወጣት የሀገሩን ታሪክ በአዲስ ብዕርና ብራና እየጻፈ ይገኛል። ሀገራችንን የኋሊት ጠፍንገው የያዟትን አጓጉል ልማዶች፣ አላስፈላጊ ንትርኮች፣ ጭቅጭቅ እና ግጭቶች በመራቅ የአሁን ወጣት በልማት ላይ አተኩሯል፣ ድህነትን ተጠይፏል። የመደመር መንግሥት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና የአመራርነት ሚና ለማጠናከር በትኩረትና በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል። ‎ ‎ሀገራዊ ርዕያችንን ዕውን ለማድረግ ሁላችሁም በንቃት እየተጋን፣ በፍቅር እንድንመላለስ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

Read the full story at abiyahmedaliofficial ↗
AdYour ad here[email protected]