ማዳጋስካር በቅኝ ግዛት ዘመን በውጭ ሀገራት ዜጎች ስም የተመዘገቡ መሬቶችን ልትወርስ ነው።

TIKVAHETHMAGAZINEneutral2026-08-12 12:33:44 UTC
AdYour ad here[email protected]

ማዳጋስካር በቅኝ ግዛት ዘመን በውጭ ሀገራት ዜጎች ስም የተመዘገቡ መሬቶችን ልትወርስ ነው። በህንድ ውቅያኖስ ላይ የምትገኘው የአፍሪካ ደሴት ሀገር ማዳጋስካር፣ በቅኝ ግዛት ዘመን በውጭ ሀገራት ዜጎች ስም ተመዝግበው የቆዩ መሬቶችን ወደ መንግሥት ይዞታነት ለማዛወር የሚያስችላትን አዲስ ሕግ አጽድቃለች። ሕጉ ማዳጋስካር ከፈረንሳይ ነፃነቷን ያገኘችበትን ሰኔ 26 ቀን 1960 እ.ኤ.አ. እንደ መነሻ ሲቆጥር፥ ከዚያ ቀን በፊት በውጭ ሀገር ዜጎች ስም የተመዘገቡ እና እስከዛሬ ድረስ ለሀገር ውስጥ ዜጎች ያልተላለፉ መሬቶች ወደ መንግሥት ይዞታነት ይዛወራሉ ተብሏል። ሕጉ፥ በዲፕሎማቲክ እና የቆንስላ ቦታዎች፣ ከነፃነት ቀን በፊት ለሀገር ውስጥ ዜጎች የተላለፉ መሬቶች እንዲሁም የማዳጋስካር ዜግነት አግኝተው በይፋ የተመዘገቡ የውጭ ዜጎች ይዞታዎች ከዚህ ሕግ ነፃ ተደርገዋል።…

Read the full story at tikvahethmagazine ↗
AdYour ad here[email protected]