ክብረት ይስጥልን‼

WASULIFEneutral2026-11-02 16:08:24 UTC
AdYour ad here[email protected]

ክብረት ይስጥልን‼ ከትናንት በስቲያ የአማራ ክልል መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጋሻው አወቀና ልዑካቸው ወሎ ኮምቦልቻ መገኘታቸውን ጠቅሰን የህዝብ ብሶት ያለበትን የገራዶ መነሃሪያ ቢጎበኙ የሚል ወንድማዊ ጥሪ አቅርበን ነበር። ትናንት ከሰዓት በኋላ ከክቡር ከንቲባው አቶ ዱባለ አብራሬ ጋር በቦታው ተገኝተው መጎብታቸው ታውቋል።ክብረት ይስጥልን።በቦታው መገኘታችሁ የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ የሄዳችሁበት ርቀት አካል ነውና እናመሰግናለን። ከጉብኝቱ በኋላ ምን ተባለ የሚለው ለጊዜው ባይታወቅም ምላሹ ተግባራዊ ለውጥ የሚያመጣ ሊሆን እንደሚችል በተስፋ እየተጠበቀ ነው።ለማንኛውም ወንድማችን ዶክተር ጋሻውንና ክቡር ከንቲባን እናመሰግናለን።ከባልደረቦቻችሁ ጋር በመናበብ ለውጤት እንደምታበቁት ተስፋ አለን‼ https://t.me/wasulife/54885?single Cc…

Read the full story at wasulife ↗
AdYour ad here[email protected]