የዋና ሥራ አስፈጻሚው የሥራ ዘመን በድጋሚ ተራዘመ
የዋና ሥራ አስፈጻሚው የሥራ ዘመን በድጋሚ ተራዘመ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው ለተጨማሪ አንድ ዓመት በኃላፊነታቸው እንዲቆዩ ውሳኔ አሳለፈ። ይህ ውሳኔ የተደረገው አየር መንገዱ የጀመራቸውን ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶች እና የ2035 የእድገት እቅድ ስኬታማ ለማድረግ ሲባል የሥራ አመራር መረጋጋትን ለመጠበቅ ነው። አቶ መስፍን ከዚህ ቀደም የጡረታ እድሜያቸው ቢደርስም፣ ቦርዱ ባደረገላቸው የውል ማራዘሚያ መሠረት አየር መንገዱን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲመሩ ቆይተዋል። አሁን በተደረገው አዲስ ውሳኔ መሠረትም እስከ 2019 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ ተቋሙን መምራታቸውን ይቀጥላሉ። ይህ የሥራ ዘመን ማራዘሚያ አየር መንገዱ አስደናቂ ዕድገት እያስመዘገበ ባለበት ወቅት የተሰጠ ነው። አቶ መስፍን በቢሾፍቱ የሚገነባውን አዲስ ግዙፍ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን…
Read the full story at addis_news ↗