አጋዝእተ ዓለም ሥላሴ ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልሉን፤ የልባችንን መልካም መሻትም ይሙሉልን🙏
አጋዝእተ ዓለም ሥላሴ ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልሉን፤ የልባችንን መልካም መሻትም ይሙሉልን🙏 በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 11፥1-9 እና በቅዱሳት አዋልድ መጻሕፍት ተጽፎ እንደምናገኘው ከጥፋት ውሃ በኋላ የኖኅ የትውልድ ነገዶች ከምሥራቅ ተነሥተው በሄዱ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚያም ተቀመጡ፤ ወልደው ተዋልደው ብዙዎች ሆኑ፡፡ በኋላም “ሳንሞት ስም ማስጠሪያ ግንብ እንገንባ” ብለው መከሩ፡፡ አለቃቸው ናምሩድም “ሞትን የሚያመጡብን ሥላሴ ናቸውና እነርሱን ወግተን ሞትን እናርቅ” አላቸው፡፡ ይህንም ለማድረግ ሰማይ ጠቀስ ግንብ ይገነቡ ጀመር፡፡ እግዚአብሔርም አለ “ኑ እንውረድ አንዱ አንዱን እንዳይሰማው በዚያ ቋንቋቸውን እንገለባብጠው”፡፡ ቅድስት ሥላሴ ምሕረታቸው የበዛ ቢሆንም በሕዝቡ ላይ ዲያብሎስ ስለሠለጠነባቸውና ለሌሎች ከሀድያን ትምህርት ይሆን ዘንድ ቋንቋቸውን…
Read the full story at addis_news ↗