በጎፋ ዞን በአንድ ሳምንት ጊዜ ዉስጥ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸው ተነገረ።

ZENA24NOWneutral2026-08-13 10:15:38 UTC
AdYour ad here[email protected]

በጎፋ ዞን በአንድ ሳምንት ጊዜ ዉስጥ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸው ተነገረ። በዞኑ በሰኔ ወር የወባ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ እንደነበር ለብስራት ሬዲዮ የተናገሩት የጎፋ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ተወካይ ወ/ሮ ሣራ አበባዉ ሰፊ ርብርብ ተደርጎ የስርጭት መጠኑን መቀነስ መቻሉን ገልፀዋል ። ባለፈው ሳምንት 5 ሺህ 194 ሰዎች በወባ በሽታ ተጠቅተዉ እንደነበር የሚገልፁት ወ/ሮ ሳራ የስርጭት ምጣኔዉ በ16 በመቶ ቀንሶ በዚህ ሳምንት ዉስጥ 4ሺህ 361 ሰዎች የወባ በሽታ ተገኝቶባቸዋል ብለዋል ። መምሪያዉ የበሽታውን ስርጭት ለመቀነስ ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑ ተጠቁሟል ። ከፍተኛ ስርጭት በታየባቸው አምስት ወረዳዎች በተለይም በሁባ ደብረ ፀሀይ እና ዛላ ወረዳዎች ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል ። በተጨማሪም የኬሚካል ርጭት በየቤቱ መካሄዱ…

Read the full story at zena24now ↗
AdYour ad here[email protected]