ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል፤ ልዩነቶች እየከረሩ ነው!

ADDIS_NEWSneutral2026-08-13 11:44:44 UTC
AdYour ad here[email protected]

ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል፤ ልዩነቶች እየከረሩ ነው! የአማራ ክልል የማህበረሰብ ክፍሎችን ወክለው በምክክሩ እየተሳተፉ የሚገኙ ተመካካሪዎች፤ ለኮሚሽኑ ቅሬታቸውን ማቅረባቸውን ምንጮች ነግረውናል። ተመካካሪዎች ፊርማቸውን ያኖሩበት የቅሬታ ደብዳቤ፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፤ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ እና ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሒሩት ገብረሥላሴ በተገኙበት ነሐሴ 05 ቀን ለኮሚሽኑ ቀርቧል። የቅሬታ ደብዳቤውን እንዲሁም ተመካካሪዎች በቃል ያቀረቡትን ቅሬታ የተቀበሉት ኮሚሽነሮቹ፤ “ተወያይተን” መልስ እንሰጣለን ማለታቸውን ሰምተናል። ዋዜማ @Addis_News @Addis_News

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]