ታሪካዊው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉዞ ሦስት አራተኛውን ምዕራፍ በስኬት አጠናቋል።
ታሪካዊው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉዞ ሦስት አራተኛውን ምዕራፍ በስኬት አጠናቋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባቀደውና በተጠበቀው ልክ ሂደቱን በስኬት እያካሄደ እንደሚገኝና አጠቃላይ የሥራውን ሦስት አራተኛ ማጠናቀቁን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ አብራርተዋል። ኮሚሽነሯ የሂደቱን ደረጃ አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ እያንዳንዳቸው 500 ተመካካሪዎችን ያቀፉ ስምንት የምክክር ቡድኖች ጥልቅ ውይይት ሲያካሂዱ መቆየታቸውን ገልጸዋል። አብዛኞቹ ቡድኖችም በተነሱ የምክረ ሀሳቦች ላይ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ እና ፊርማቸውን በማኖር ሥራቸውን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ። በውይይት ሂደቱ ውስጥ አለመግባባቶችና የሃሳብ ግጭቶች ቢያጋጥሙም፣ እነዚህ ሁኔታዎች መከሰታቸው የምክክሩን አስፈላጊነት ይበልጥ ያረጋገጠ መሆኑን ኮሚሽነሯ አስገንዝበዋል። ተመካካሪዎቹ ልዩነቶቻቸውን…
Read the full story at amharamassmedia ↗