ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፤ምልጃው እና ረድኤቱም አይለየን🙏
ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፤ምልጃው እና ረድኤቱም አይለየን🙏 ድርሳነ ሩፋኤል ላይ ተጽፎ እደምናገኘው 7 ሊቃነ መላዕክት ሲኖሩ አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው፤ የስሙ ትርጓሜም “እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው” ማለት ነው። ከእግዚአብሔር ዙፋን ስር ትዕዛዝ በወጣ ግዜ ኪሩቤል ተቀብለው ለሱራፌል ያስተላልፋሉ፤ ሱራፌልም ለሚካኤልና ለገብርኤል ለሩፋኤልም ያደርሳሉ፡፡ ሚካኤል ለፍጥረቱ በጎም ይሁን ክፉ ትዕዛዙን ይፈጽሙ ዘንድ መላዕክትን ያዛቸዋል፤ ኪሩቤልና ሱራፌል መላዕክቱም ሁሉ አቤቱ የእጅህን ስራ አታጥፋ እያሉ ቀንና ከማታ ይለምናሉ። የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከዲያቢሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ እግዚአብሔር ይገስፅህ አለው እንጂ የስድብን ቃል አልተናገረውም ሲባል ሰምተናል፡፡ ሊቀ ነብያት ሙሴ እጅግ ታዛዥና የዋህ ስለነበርና ከንዓንን ለማየት ወደ ናባው ተራራ…
Read the full story at addis_news ↗