የአዲስ አበባ ጉዳይ ከስምምነት እንደተደረሰበት ተገለጸ

ADDIS_NEWSneutral2026-08-13 14:03:01 UTC
AdYour ad here[email protected]

የአዲስ አበባ ጉዳይ ከስምምነት እንደተደረሰበት ተገለጸ በተመካካሪዎች ዘንድ በሰፊው አከራካሪ ከነበሩ አጀንዳዎች መካከል የፌደራል ከተሞች፡- የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ጉዳይ ዋነኛው ሲሆን፣ በዛሬው የምክክር ውሎ በአጀንዳው ላይ ስምምነት ላይ እንደተደረሰ ተገልጿል። ከሐምሌ 8/2018 ዓ.ም. ጀምሮ በይፋ በተጀመረው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 4 ሺህ ተመካካሪዎች በተመረጡ 8 አጀንዳዎች ላይ ሲመክሩ መቆየታቸው ይታወቃል። በዛሬው የምክክር ጉባኤ ውሎ በተመካካሪዎች ዘንድ በሰፊው አከራካሪ የነበረው የፌደራል ከተሞች፡- የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ጉዳይ አጀንዳ ስምምነት እንደተደረሰበት ታውቋል። በዚህ መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ የፌደራል እና የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ እንድትሆን 500 አባላት ያሉት የተመካካሪዎች ቡድን ተስማምተዋል። ልዩ ጥቅምን በተመለከተ ዝርዝር ጉዳዮች በቀጣይ በሰፊው…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]