ድርቅ‼️‼

AYUZEHABESHANEWSneutral2026-08-13 17:44:30 UTC
AdYour ad here[email protected]

ድርቅ‼️‼ በሰሜን ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው ከባድ የድርቅ አደጋ ምክንያት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የቤት እንስሳት እያለቁ መሆናቸውን ከየአካባቢው የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል። በትግራይ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች፣ በአማራ ክልል ዋግምራ ዞን፣ በሰሜን ጎንደር ጠለምትና የበየዳ ቆላማ አካባቢዎች እንዲሁም በሰሜን ወሎ በተለያዩ ቦታዎች የክረምት ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት የቁም እንስሳት እልቂት ይበልጥ እየከፋ መጥቷል። በተለይም በሰሜን ጎንደር ጠለምት ቀጠና ከአስራ አንድ ሺህ (11,000) በላይ የቀንድና የጋማ ከብቶች እንዲሁም የበግና ፍየሎች ማለቃቸው ታውቋል። በሌላ በኩል በትግራይ ክልል በአብዛኞቹ አካባቢዎች በዚህ ክረምት የተዘራና የበቀለ እህል ጨርሶ አለመኖሩን የአዩዘሀበሻ የመረጃ ምንጮቻች ገልጸዋል። የድርቁ ስፋትና የሚያሳድረው ተፅዕኖ በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች…

Read the full story at ayuzehabeshanews ↗
AdYour ad here[email protected]